የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ግድያ ክትትል እየተደረገበት እንደኾነ ጽ/ቤቱ አስታወቀ

Channel:
Subscribers:
200,000
Published on ● Video Link: https://www.youtube.com/watch?v=X5e6jEGB2c0



Duration: 2:52
59 views
0


- ቋሚ ሲኖዶስ ለምእመናንና ለተቋማቱ መንግሥት የደኅንነት ዋስትና እንዲሰጥ ጠየቀ

ባለፈው ሳምንት እሑድ ማለዳ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ በነበሩት በኩረ ትጉሃን ዘርዐ ዳዊት ኃይሉ ላይ፣ በጎንደር ከተማ ግድያ የፈጸሙ ተጠርጣሪዎችን ለማግኘት መንግሥት እየሠራ እንደሚገኝ፣ የሀገረ ሰብከቱ ጽ/ቤት ሲያስታውቅ፤ ቋሚ ሲኖዶስም፣ በምእመናንና በተቋማት ላይ እየተባባሱ ካሉ ጥቃቶች መንግሥት የደኅንነት ዋስትና እንዲሰጥ ጠይቋል፡፡

የሀገረ ስብከቱ ጸሐፊ በኵረ ሥዩማን ዐይንሸት ሞገስ፣ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ ዋና ሥራ አስኪያጁ የተገደሉት፣ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ወደ እንፍራንዝ ለመሔድ በጽ/ቤቱ በር ላይ ቆመው በነበሩበት “ያልታወቁ ሰዎች” ሲሉ በገለጿቸው ግለሰቦች ተኩስ ነው፡፡

በሌላ በኩል፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቋሚ ሲኖዶስ፣ ትላንት ሰኞ በሰጠው መግለጫ፣ በቅርቡ፣ ከ60 በላይ አገልጋዮች እና ምዕምናን እንደተገደሉበት አስታውቋል፡፡

በንጹሐን ምእመናንና ተቋማቷ ላይ ያተኮሩ ጥቃቶች፣ “በሰማይም በምድርም ያስጠይቃሉ” ያለው ቋሚ ሲኖዶሱ፣ በአስቸኳይ እንዲቆሙና መንግሥትም የደኅንነት ዋስትና እንዲሰጥ ጠይቋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።




Other Videos By VOA Amharic


2023-12-13አቶ ታየ ደንዳአ ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ ባለቤታቸው ተናገሩ
2023-12-12ጋቢና ቪኦኤ
2023-12-12ከምሽቱ 3:00 የአማርኛ ዜና
2023-12-12ከምሽቱ 3:00 የአማርኛ ዜና
2023-12-12“አስቸኳይ ምላሽ ለትግራይ” ክልል አቀፍ ኮሚቴ ሀብት የማሰባሰብ ንቅናቄውን በይፋ ጀመረ
2023-12-12የትግራይ ክልል የኢሚግሬሽን ሠራተኞች ከሁለት ዓመታት በላይ ደሞዛቸው መቋረጡን ተናገሩ
2023-12-12የሀገር ውስጥ ምርቶች ተፈላጊነት መጨመር በጥራታቸው መሻሻል ወይስ በዋጋቸው?
2023-12-12ዓመቱን ሲወዛገቡ ያሳለፉት ዩናይትድ ስቴትስ እና ቻይና መሪዎቻቸው ኅዳር ላይ ተነጋግረዋል
2023-12-12የዐማራ ክልል ግጭት ሠራተኛውን ዋስትና እያሳጣው እንደኾነ ኮንፈዴሬሽኑ አስታወቀ
2023-12-12እስራኤላውያን ሰፋሪዎች በአሜሪካ የቪዛ እገዳ እንደተበሳጩ ገለጹ
2023-12-12የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ግድያ ክትትል እየተደረገበት እንደኾነ ጽ/ቤቱ አስታወቀ
2023-12-12የመከላከያ ኀይሉ በሀገር ውስጥ ግጭቶች ድሮን መጠቀሙን እንደሚቀጥል አስታወቀ
2023-12-11ጋቢና ቪኦኤ
2023-12-11ከምሽቱ 3:00 የአማርኛ ዜና
2023-12-11የአመጋብ ዘይቤያችን፣ በሆድ ዕቃችን የሚላወሱት ረቂቅ ተሕዋስያን እና ጤናችን
2023-12-11በታንዛኒያ እና ዩጋንዳ “ነዋሪዎችን ያስፈራራል” የተባለው የነዳጅ ኩባንያ ተቃውሞ ገጠመው
2023-12-11ዩናይትድ ስቴትስ የጸጥታው ምክር ቤት የጋዛ እስራኤል ተኩስ አቁም ውሳኔዋን አብራራች
2023-12-11ግጭቶችን በድርድር ለመፍታት መንግሥት ተነሣሽነቱን እንዲወስድ የመብቶች ተሟጋቾች ጠየቁ
2023-12-11በወለጋ ዞኖች የጸጥታ ችግር የደረሰ የቡና ምርት ለመሰብሰብ እንደተቸገሩ አርሶ አደሮች ገለጹ
2023-12-11በደቡብ ወሎ ዞን ሰላማውያን ሰዎች በድሮን ጥቃት እንደተገደሉ ነዋሪዎች ተናገሩ
2023-12-08ጋቢና ቪኦኤ