በሜሪላንድ ቦልቲሞር አቅራቢያ አንድ ትልቅ ድልድይ ተደርምሶ ጉዳት አደረሰ
በዩናይትድ ስቴትስ ምስራቃዊ ክፍለ ግዛት ሜሪላንድ ውስጥ በሚገኘው የባልቲሞር ከተማ አቅራቢያ ዛሬ ማክሰኞ ፍራንሲስ ስኮት ኪ ብሪጅ የተባለው አንድ ትልቅ ድልድይ ተደርምሶ ወድቋል፡፡
በድልድዩ ላይ ወድቆ በነበረበት ወቅት በርካታ ተሽከርካሪዎች በድልድዩ ላይ እንደነበሩ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
የነፍስ አድን ሠራተኞች ሁኔታቸው ያልታወቀ ሰባት ሰዎችን ፍለጋ ላይ መሆናቸውን ባለሥልጣናት ገለጸዋል።
አደጋው የደረሰው ፓታፕስኮ በተባለው ወንዝ ውስጥ የነበረውና ዳሊ የተባለው የሲንጋፖርን ባንዲራ የሚያውለበልብ እቃ አጓጓዥ መርከብ ከድልድዩ ደጋፊ አምድ ጋር በመጋጨቱ ነው፡፡
የባልቲሞር ከተማ የእሳት አደጋ መከላከያ ኃላፊ ጄምስ ዋላስ አደጋው ከደረሰ ሰዓታት በኋላ ሁለት ሰዎች ከውሃ ውስጥ እንዲወጡ መደረጉን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡
ከሁለቱ ሰዎች መካከል አንደኛው ከባድ ጉዳት ያገኛቸው በመሆኑ ወደ ህክምና ማዕከል ሲወሰዱ ሌላኛው ላይ ምንም ጉዳት አልደረሰም፡፡
የነፍስ አድን ጠላቂዎች ከ9 ዲግሪ በታች ከሆነው ከወንዙ ውሃ ቅዝቃዜ ጋር በመጋፈጥ ሁኔታቸው ያልታወቁ ሌሎች ሰዎችን እያፈላለጉ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የሜሪላንድ አገረ ገዥ ዌስ ሙር የአስቸኳይ ጊዜ አውጀዋል፡፡
ክፍለ ግዛቱ ከባይደን አስተዳደርና ከሌሎች የአስቸኳይ ነፍስ አድን ቡድኖች ጋር በመሆን የፌደራል ኃይሎችን በፍጥነት አሰማርቶ እየሰራ መሆኑንም አገረ ገዥው ተናግረዋል፡፡
የባልቲሞር ከንቲባ ብራንደን ስኮት ክስተቱን "የማይታሰብ አሳዛኝ" ብለውታል።
የባልቲሞር ፖሊስ ኮሚሽነር ሪቻርድ ዎርሊ ከድልድዩ ምሶሶ ጋር የተፈጠረው የመርከቡ ግጭት ሆን ተብሎ የተደረገ ስለመሆኑ "ምንም ምልክት የለም" ብለዋል።
ከድልድዩ አንደኛው ምሶሶ ጋር የተጋጨውን መርከብ ይመሩ የነበሩት ሁለቱ የመርከቡ ካፕቴኖችን ጨምሮ ሁሉም የመርከቢቱ ሠራተኞች ምንም አደጋ ያላገኛቸውና በደህና ሁኔታ ላይ መሆናቸውን የዳሊ መርከብ ባለቤት የሆነው የሲነርጂ ማሪን ኮርፕ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
47 ዓመቱን ያስቆጠረውና 2.5 ኬሎሜትሮች ርዝመት ያለው ድልድይ፣ በዩናይትድ ስቴትስ ከሚገኙ ትላልቅ የወደብ ከተሞች አንዷ የሆነችው ባልቲሞር ከተማን በመዞር ወደ ተለያዩ ክፍለግዛቶች የሚወስዱ ትላልቅ አውራጎዳናዎችን የሚያገናኝ ነው፡፡
“ኪ ብሪጅ” እየተባለ ባጭሩ የሚጠራው ድልድይ የተሰየመው የዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ መዝሙር “The Star Spangled Banner,” የተባለውን ግጥም በጻፈው ፍራንሲ ስኮት ኪ (Francis Scott Key) ስም ነው፡፡
ስኮት ግጥሙን የጻፈው እኤአ ከ1812 ጀምሮ በሀገራት መካከል የተጀመረውን ጦርነት ተከትሎ የእንግሊዝ ጦር እኤአ በ1814 ባልቲሞር በነበረው ትልቅ የአሜሪካ ምሽግ ላይ የሰነዘረውን ከባድ የቦምብ ጥቃት ከተመለከተ በኋላ ነው፡፡
- - - - - - - - - -- - - - - - - - - -- - - - - - - - - -- - - - - - - - - -
📜 ቪኦኤ-አማርኛ ስለ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ አፍሪካ፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና ዓለም አቀፍ በዲጂታል፣ በራዲዮና በቴሌቪዥን ዜናና ዘገባዎችን ለአድማጭና ለተመልካች ያቀርባል።
VOA Amharic reaches our audience on digital, radio, and TV, delivering news and content about Ethiopia, Eritrea, Africa and United States. We will also be bringing you Health Shows, Youth Shows, Democracy Field, Women’s Shows, Sports Shows on different days, stay tuned.
🔷 የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ሊንኮችን በመጫን ይከተሉን።
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/voaamharic
ኢንስታግራም - https://www.instagram.com/voaamharic
X - https://x.com/VOAAmharic
ዌብሳይት - https://amharic.voanews.com
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ፡- https://www.youtube.com/voaamharic
የስልክ መሥመራችን 202-205-9942 የውስጥ መሥመር 14 ነው።
Other Videos By VOA Amharic
2024-03-28 | ጋቢና ቪኦኤ |
2024-03-27 | አሜሪካዊው ጋዜጠኛ በሩስያ እስር ቤት አንድ ዓመት ሞላው |
2024-03-27 | ከምሽቱ 3:00 የአማርኛ ዜና |
2024-03-26 | የምዕራቡ ዓለም ለኒውክሌር ማመንጫ ጣቢያዎቹ አሁንም የሩስያ አቅርቦት ጥገኛ ነው |
2024-03-26 | በአማራ ክልል የጎብኝዎች ቁጥር በእጅጉ ማሽቆልቆሉ ተገለጸ |
2024-03-26 | ፖል ቢያ ለምርጫ እንዲወዳደሩ ደጋፊዎቻቸው ጥሪ አቀረቡ |
2024-03-26 | ከምሽቱ 3:00 የአማርኛ ዜና |
2024-03-26 | የአማራ ክልል ግጭት በድርድር ተቋጭቶ የምክክር ሒደቱ እንዲቀጥል ኮሚሽኑ ጠየቀ |
2024-03-26 | ጋቢና ቪኦኤ |
2024-03-26 | ንግድ ባንክ ከተወሰደበት ገንዘብ እስከ አሁን 80 በመቶውን እንዳስመለሰ ተገለጸ |
2024-03-26 | በሜሪላንድ ቦልቲሞር አቅራቢያ አንድ ትልቅ ድልድይ ተደርምሶ ጉዳት አደረሰ |
2024-03-26 | ጋቢና ቪኦኤ |
2024-03-26 | ጋቢና ቪኦኤ |
2024-03-25 | ከምሽቱ 3:00 የአማርኛ ዜና |
2024-03-25 | ትረምፕ እና ባይደን በዚህ ሣምንት |
2024-03-25 | በአማራ ክልል ለማስተማሪያ በዋለ የመማሪያ መጽሐፍ ላይ ቅሬታ ቀረበ |
2024-03-25 | ለስልታዊ እና ተደጋጋሚ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጥ ኢሰመኮ ጠየቀ |
2024-03-25 | የጋርዱላ ዞን ከእገታ የተለቀቁ የቀን ሠራተኞችን መረከቡን አስታወቀ |
2024-03-22 | ጋቢና ቪኦኤ |
2024-03-22 | የሩሲያ ወታደራዊ ተጽኖ በአፍሪካ |
2024-03-22 | የኅትመት ዋጋ እና የሳተላይት ክፍያ መናር |