ኒው ዮርክ የደረሱት የሴኔጋል ፍልሰተኞች ፈተና

Channel:
Subscribers:
140,000
Published on ● Video Link: https://www.youtube.com/watch?v=RsB1MtIEWUo



Duration: 0:50
343 views
2


ከሁለት ዓመታት በፊት ጀምሮ፣ ከቬንዙዌላ እና ከሌሎችም የላቲን አሜሪካ አገራት በመጡ ፍልሰተኞች የተጥለቀለቀቸው የኒው ዮርክ ከተማ፣ ባለፈው አንድ ዓመት ደግሞ በሶስት እጥፍ ጭማሪ ያሳዩቱንና ከምዕራብ አፍሪካ የመጡትን ፍልሰተኞች በማስተናገድ ላይ ትገኛለች።
ሃርለም በተሰኘው የኒው ዮርክ ክፍለ ከተማ፣ ከምዕራብ አፍሪካ የመጡ ፍልሰተኞች የአገራቸውን ምግብ በሚያገኙበት አንድ ምግብ ቤት ተሰባስበዋል። “ትንሿ ሴኔጋል” ብለው የሚጠሯት ሰፈር፣ አዲስ የመጡትን ፍልሰተኞች ሞቅ አድርጋ በመቀበል ላይ ነች፡፡ ፍልሰተኞቹ እዚህ ለመድረስ በርካታ ወሮ በላ ቡድኖችን እና አድካሚ ጎዞን አልፈዋል።
ማማዱ፣ አዲስ ከደረሱት ፍልሰተኞች አንዱ ነው።
“ከሴኔጋል ነው የመጣሁት። በሞሮኮ፣ ስፔን፣ ኒካራጓ፣ ኤል ሳልቫዶር እና ሜክሲኮ አድርጌ ነው የመጣሁት፡፡ በርካታ አዘዋዋሪዎች ገጥመውናል። ሽጉጥ ጭንቅላታችን ላይ ደቅነው ገንዘብ አምጡ ይሉናል። ገንዘብ ከሌለህ፣ ሌሎች ያሉህን ነገሮች ሁሉ ይወስዳሉ። በጣም ከባድ ነበር።” ብሏል፡፡
ፍልሰተኞቹ አሜሪካ ከደረሱ በኋላ፣ አስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ገጥሟቸዋል። በአሜሪካ የጠበቁትን አላገኙም።
ማማዱ ድራሜ፣ የትውልደ ሴኔጋል አሜሪካውያን ማኅበር ፕሬዝደንት ናቸው።
“ሁሉም ወደ አሜሪካ ከመምጣቱ በፊት፣ ይህን አገር የሚያስበው፣ በቃ ካለ ችግር በተሻለ ሁኔታ እንደሚኖርበት አድርጎ ነው። እውነታው ግን፣ እዚህ ከደረሱ በኋላ የሚገጥማቸው ከጠበቁት የተለየ ሁኔታ ነው።” ብለዋል፡፡
እነዚህ ፍልሰተኞች የሥራ ፈቃድ ለማግኘት ከ90 እስከ 150 ቀናት መጠበቅ አለባቸው። ይህም ብዙዎቹ ስለ ወደፊቱ ሕይወታቸው እርገጠኞች እንዳይሆኑ አድርጓል።
ከሴኔጋል የመጣው አዲስ ፍልሰተኛ፣ የሥራ ፈቃድ ጥበቃ ላይ በመሆኑ ስሙን መግልጽ አልፈለገም።
“ችግራችንን በተመለከተ ልንነግራችሁ ነው እዚህ ያለነው። መሥራት ነው የምንፈልገው። የሥራ ፈቃድ ማግኘት ነው የምንፈልገው። ያንን ካገኘን፣ ወደ ምንሄድበት እንሄዳለን።” ብሏል፡፡

የአሜሪካንን ፀጋ ለማግኘት ፍለጋ ላይ ያሉት እነዚህ አዲስ ፍልሰተኞች፣ አሁን በአገሪቱ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ አሳሳቢ ሆኖባቸዋል። በተለይም፣ የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ በምረጡኝ ዘመቻዎቻቸው ወቅት፣ ወደ አገሪቱ በሕገ ወጥ መንገድ የገቡ ፍልሰትኞችን በተመለከተ የሚያሰሙት ንግግር ያሳስባቸዋል።
በድጋሚ የትውልደ ሴኔጋል አሜሪካውያን ማኅበር ፕሬዝደንቱ ማማዱ ድራሜ።
“አብዛኞቹ ፍልሰተኞች ትረምፕ የሚናገሩት ነገር ያሳስባቸዋል። በተለይም በጅምላ ከአገር ስለማስወጣት የተናገሩት በጣም ያሳስባቸዋል። ፍልሰተኖቹ በአሜሪካ አሁን ያለውን የፖለቲካ ሁኔታ ያውቃሉ።” ብለዋል፡፡
በክፍለ ግዛቱ የዲሞክራቲክ ፓርቲ የሴኔት አባል የሆኑት ኮርዴል ክሊር፣ በኒው ዮርክ የምዕራብ ሃርለምን ክፍለ ከተማ ይወክላሉ። እርሳቸው እንደሚሉት፣ የፍልሰተኞች ጉዳይ የፓርቲ ጉዳይ አይደለም። የፌዴራል መንግስቱን እገዛም ይሻል።
“በርካታ ፍልሰተኞች የገቡባቸው፣ እንደ ኒው ዮርክ ያሉ ክፍለ ግዛቶች፣ ከፌዴራል መንግስቱ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት አለባቸው።” ብለዋል፡፡
የምርጫው ወቅት እየተቃረበ እና የአዲሶቹ ፍልሰተኞች ሁኔታ የመገናኛ ብዙሃን ትኩረትን እየሳበ ባለበት ወቅት፣ ለእነርሱ ዋናው አንገብጋቢው ጉዳይ፣ በተለይም በሴንጋላውያን ማኅበረሰብ እገዛ፣ የተሻለን ሕይወት መኖር ነው።




Other Videos By VOA Amharic


2024-03-25በአማራ ክልል ለማስተማሪያ በዋለ የመማሪያ መጽሐፍ ላይ ቅሬታ ቀረበ
2024-03-25ለስልታዊ እና ተደጋጋሚ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጥ ኢሰመኮ ጠየቀ
2024-03-25የጋርዱላ ዞን ከእገታ የተለቀቁ የቀን ሠራተኞችን መረከቡን አስታወቀ
2024-03-22ጋቢና ቪኦኤ
2024-03-22የሩሲያ ወታደራዊ ተጽኖ በአፍሪካ
2024-03-22የኅትመት ዋጋ እና የሳተላይት ክፍያ መናር
2024-03-22ግዙፉ የቴክሳስ ኤል ፓሶ የፍልሰተኞች ማቆያ ማዕከል
2024-03-22የአስቸኳይ ጊዜ ታሳሪዎች በደብዳቤ አቤቱታ አቀረቡ
2024-03-22የታገቱት የቀን ሠራተኞች ተለቀቁ
2024-03-22ከምሽቱ 3:00 የአማርኛ ዜና
2024-03-22ኒው ዮርክ የደረሱት የሴኔጋል ፍልሰተኞች ፈተና
2024-03-22ጋቢና ቪኦኤ
2024-03-22ጋቢና ቪኦኤ
2024-03-21ጋቢና ቪኦኤ
2024-03-21በጊዳ አያና ወረዳ አሥር ሲቪሎች ላይ የበቀል ግድያ መፈጸሙ ተገለጸ
2024-03-21መጪው የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ እና የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ችግር
2024-03-21ኒው ዮርክ የደረሱት የሴኔጋል ፍልሰተኞች ፈተና
2024-03-21ከምሽቱ 3:00 የአማርኛ ዜና
2024-03-21ጋቢና ቪኦኤ
2024-03-20ሴትነትና አካል ጉዳት ያልበገራቸው የምክር ቤት አባል ሊዲያ አሰፋ ዳውሰን
2024-03-20ጋቢና ቪኦኤ



Tags:
Voice of America
VOA
VOA Amharic
Amharic
Ethiopia
Ethiopia News
Amhara
Oromia
Tigray