ህወሓት የካድሬዎች ስብሰባውን ከሁለት ሳምንት በኋላ ለማካሔድ ወሰነ
Channel:
Subscribers:
142,000
Published on ● Video Link: https://www.youtube.com/watch?v=d7Ca7nXaakg
በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ክልከላ የተደረገበት የህወሓት ስብሰባ፣ ከሁለት ሳምንታት በኋላ እንዲካሔድ፣ የፓርቲው ተሰብሳቢ ካድሬዎች ትላንት ወስነዋል፡፡
የስብሰባውን ውሳኔ አስመልክቶ፣ ህወሓት ትላንት እሑድ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ በፓርቲው ካድሬዎች ላይ በወሰደው ርምጃ እርምት እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡
የጊዜያዊ አስተዳደሩ የኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት መልስ፣ “የስብሰባው ተሳታፊዎች ስክነት እና ማስተዋል የጎደለው ተቀባይነት የለሌው ሥራ ነው የፈጸሙት፤” ሲሉ ተችተዋል፡፡ አሁንም፣ መንግሥት ርምጃ መውሰድ በሚገባው ጊዜ ርምጃ ይወስዳል፤ ሲሉም በአጽንዖት አስታውቀዋል፡፡
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡