ታንዛኒያ ከዱባይ ኩባንያ ጋራ አወዛጋቢ የወደብ አስተዳደር ስምምነት ተፈራረመች

Channel:
Subscribers:
142,000
Published on ● Video Link: https://www.youtube.com/watch?v=qQkw7Cs5sP0



Duration: 1:28
122 views
3


የታንዛኒያ መንግሥት፣ መቀመጫውን በዱባይ ካደረገው ዲፒ ወርልድ ዓለም አቀፍ የሎጂስቲክ ኩባንያ ጋራ የተፈራረመው የወደብ ስምምነት፣ ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሥቷል፤ በደርዘን የሚቆጠሩ ተቺዎችም ለእስር ተዳርገዋል።

ታንዛኒያ፣ ከዲፒ ወርልድ ጋራ ስምምነት የፈጸመችው፣ ፕሬዚዳንቷ ሳሚያ ሱሉሁ ሐሰን በተገኙበት ነው፡፡ ርእሰ ብሔሯ ሳሚያ ሱሉሁ፣ ከእርሳቸው በፊት እንደነበሩት ሟቹ ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ፣ ተቃዋሚዎችንና ተቺዎችን በማፈን ቅሬታ ይቀርብባቸዋል።

የታንዛኒያ የወደቦች ባለሥልጣን ዲሬክተር ጀነራል፣ ፕላስዱስ ምቦሳ ስለ ስምምነቱ ሲያስረዱ፤ ዲፒ ወርልድ የሚያስተዳደረው፣ የአገሪቱን ጠቅላላ ወደብ ሳይኾን፣ በንግድ መዲናዋ በዳሬ ሰላም ከተማ የሚገኘውን፣ አራት የመርከብ ማራገፊያ ቦታዎችን ብቻ እንደኾነ ገልጸዋል። ለ30 ዓመታት የሚዘልቀው የውል ስምምነቱ፣ በየአምስት ዓመቱ እንደሚገመገምም ጠቁመዋል።

ተቃዋሚዎች እና የሲቪል ማኅበረሰቦች ግን፣ የታንዛኒያ ወደቦች፣ በውጪ የሎጂስቲክ ኩባንያ እንዲተዳደር መወሰኑን ተቃውመዋል፡፡ መንግሥት በበኩሉ፣ ርምጃው የወደብ ብቃትን እንደሚያሻሽልና የአገሪቱን ኢኮኖሚ እንደሚያሳድግ አመልክቷል።

የታንዛኒያ ፓርላማ፣ እ.አ.አ ሰኔ 10 ቀን ያጸደቀው ይህ ስምምነት፣ ከፍተኛ ተቃውሞ ማሥነሳቱ እንደቀጠለ ነው፡፡ እስከ አሁን 22 ሰዎች እንደታሰሩ፣ ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ተቋም ሂዩማን ራይትስ ወች አስታውቋል። ተቋሙ፣ በነሐሴ ወር ባወጣው ሪፖርትም፣ ታንዛኒያ በነጻነት ሐሳብን የመግለጽ መብትንና የመቃወም መብትን እንድታከብር ጠይቆ ነበር።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡




Other Videos By VOA Amharic


2023-10-25የሄይቲ የዳያስፖራ ጋዜጣ ሐሰተኛ ወሬዎችን እየተዋጋ ነው
2023-10-24ጋቢና ቪኦኤ
2023-10-24የወገኔ ዓመታዊ “የርኅራኄ ምሽት”
2023-10-24ኢሰመኮ “የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ፍትሕን ተነፍገዋል” ሲል መንግሥትን ወቀሰ
2023-10-24በአሜሪካ የመካከለኛው ምሥራቅ ወታደራዊ ዝግጅት የግጭት መስፋፋት ስጋቱ አይሏል
2023-10-24የኢትዮጵያዊው የሕፃናት መጽሐፍ ዓለም አቀፍ ሽልማትን አሸነፈ
2023-10-24በናይጄሪያ በሦስት ዓመታት ውስጥ ከ800 በላይ ሰዎች ከሕግ ውጪ እንደተገደሉ ተገለጸ
2023-10-24በዐማራ ክልል የሚገኙ የኦሮሚያ ክልል የግጭት ተፈናቃዮች ሊመለሱ ነው
2023-10-24ከምሽቱ 3:00 የአማርኛ ዜና
2023-10-24በምዕራብ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች የጸጥታ ችግር በተባባሰው የወባ በሽታ ብዙዎች እየሞቱ እንደኾነ ተገለጸ
2023-10-24ታንዛኒያ ከዱባይ ኩባንያ ጋራ አወዛጋቢ የወደብ አስተዳደር ስምምነት ተፈራረመች
2023-10-24የናይጄሪያ “የመመለሻ በር” ዐውደ ትርኢት የአፍሪካ ዲያስፖራዎችን ለማስተሳሰር አልሟል
2023-10-24ዚምባብዌያውያን ከአገሪቱ የአልማዝ ኢንዱስትሪ ተጠቃሚ ለመኾን ተስፋ ያደርጋሉ
2023-10-23ጋቢና ቪኦኤ
2023-10-23በዓለም ሀገራት የልጆች እና የወጣቶች የአእምሮ ጤና ሁከት አሳሳቢ ኾኗል
2023-10-23በስፔን የአገር አቋራጭ እና የማራቶን ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ
2023-10-23ዩናይትድ ስቴትስ በመካከለኛው ምሥራቅ ወታደራዊ ዝግጁነቷን አጠናከረች
2023-10-23ከምሽቱ 3:00 የአማርኛ ዜና
2023-10-23የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር በጣልቃ ገብነት ወቀሱ
2023-10-23የብዙኀን መገናኛዎች በባለሞያዎች እስር ሥራቸውን ለማከናወን እንደተቸገሩ ም/ቤቱ ገለጸ
2023-10-23በሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው ላይ የሚሰነዘሩ ትችቶች ተገቢ እንዳልኾኑ ሚኒስትሩ ተቃወሙ