የብዙኀን መገናኛዎች በባለሞያዎች እስር ሥራቸውን ለማከናወን እንደተቸገሩ ም/ቤቱ ገለጸ

Channel:
Subscribers:
142,000
Published on ● Video Link: https://www.youtube.com/watch?v=dMlMpKd8PPM



Duration: 5:07
102 views
3


ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፣ በአንዳንድ የብዙኀን መገናኛ ተቋማት እና ጋዜጠኞች ላይ፣ ከሕግ አግባብ ውጪ አስሮ የማቆየትና ለስርጭት የተዘጋጀ የኅትመት ውጤትን የማገድ ድርጊቶች እንደተፈጸሙ የገለጸው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ምክር ቤት፣ ሥራቸውን ለማከናወን እየተቸገሩ እንደኾነ አስታወቀ፡፡

ምክር ቤቱ፣ ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ስላወጣው መግለጫ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ማብራሪያ የሰጡት የምክር ቤቱ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታምራት ኃይሉ፣ የእገዳ ድርጊቱ ተፈጽሞባቸዋል ያሏቸው ሁለት የብዙኀን መገናኛዎች፣ የዕለት ከዕለት ሥራዎቻቸው እንደተስተጓጎለ አመልክተዋል፡፡

“በጸጥታ ኀይሎች፣ ከሕግ አግባብ ውጪ ተፈጽሟል ያለው ይኸው ድርጊት እንዳሳሰበው” የጠቀሰው የምክር ቤቱ መግለጫ፣ በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅም ውስጥ ቢኾን፣ በጋዜጠኞች እና በብዙኀን መገናኛ ተቋማት ላይ የሚኖር ተጠያቂነት፣ ሕጋዊነትን የተከተለ ሊኾን እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡




Other Videos By VOA Amharic


2023-10-24በምዕራብ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች የጸጥታ ችግር በተባባሰው የወባ በሽታ ብዙዎች እየሞቱ እንደኾነ ተገለጸ
2023-10-24ታንዛኒያ ከዱባይ ኩባንያ ጋራ አወዛጋቢ የወደብ አስተዳደር ስምምነት ተፈራረመች
2023-10-24የናይጄሪያ “የመመለሻ በር” ዐውደ ትርኢት የአፍሪካ ዲያስፖራዎችን ለማስተሳሰር አልሟል
2023-10-24ዚምባብዌያውያን ከአገሪቱ የአልማዝ ኢንዱስትሪ ተጠቃሚ ለመኾን ተስፋ ያደርጋሉ
2023-10-23ጋቢና ቪኦኤ
2023-10-23በዓለም ሀገራት የልጆች እና የወጣቶች የአእምሮ ጤና ሁከት አሳሳቢ ኾኗል
2023-10-23በስፔን የአገር አቋራጭ እና የማራቶን ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ
2023-10-23ዩናይትድ ስቴትስ በመካከለኛው ምሥራቅ ወታደራዊ ዝግጁነቷን አጠናከረች
2023-10-23ከምሽቱ 3:00 የአማርኛ ዜና
2023-10-23የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር በጣልቃ ገብነት ወቀሱ
2023-10-23የብዙኀን መገናኛዎች በባለሞያዎች እስር ሥራቸውን ለማከናወን እንደተቸገሩ ም/ቤቱ ገለጸ
2023-10-23በሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው ላይ የሚሰነዘሩ ትችቶች ተገቢ እንዳልኾኑ ሚኒስትሩ ተቃወሙ
2023-10-23መንግሥት በዐማራ ክልል “አንጻራዊ ሰላም ሰፍኗል” ቢልም የጸጥታ ችግሩ እንደተባባሰ ነዋሪዎች ገለጹ
2023-10-23በዐማራ ክልል የቀጠለው ግጭት እና የግብርና አቅርቦት እጥረት የኢትዮጵያን የምግብ ዋስትና አደጋ ላይ ጥሏል
2023-10-20ጋቢና ቪኦኤ
2023-10-20የምዕራብ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች አንዳንድ ወረዳዎች የከፋ ረኀብ ተጋርጦባቸዋል
2023-10-20ፕሬዚዳንት ባይደን ስለ እስራኤል-ሐማስ ግጭት ያደረጉት ንግግር እና የባለሞያ አስተያየት
2023-10-20ከምሽቱ 3:00 የአማርኛ ዜና
2023-10-20ወደ ዩኒቨርሲቲዎቻቸው መመለስ ያልቻሉ የዐማራ ክልል ተማሪዎች “መንግሥት ያግዘን” አሉ
2023-10-20በጉራጌ እና በቀቤና ብሔረሰቦች ግጭት ከመቶ በላይ ተጠርጣሪዎች እንደተያዙ ተገለጸ
2023-10-20በኦሮሚያ ክልል በዜጎች ላይ የሚፈጸመው እገታ በመባባሱ ነዋሪዎች ከቀዬአቸው እየለቀቁ መኾኑን ተናገሩ